ማዲያትን በቤት ውስጥ እንዴት ማከም ይቻላል?

ማዲያትን በቤት ውስጥ እንዴት ማከም ይቻላል?

ብዙዉን ጊዜ ኑሮ ያጎሳቆላቸው እናቶች ላይ ይታያል… ታዲያ የእኛ እናቶች እኛን ለማሳደግ ብለው የፊታቸው ቆዳ ሲጠቁር መፍትሄ ይሆናቸው ዘንድ አንድ መላ ብንፈልግላቸውስ ብለን አሰብን፡፡ እነሆ በቀላሉ በቤት ውስጥ የሚዘጋጅ መፍትሄ ይዘን መጣን፡፡ የእናቱን ጉስቁልና ማየት የማይፈልግ ሼር ያድርግ፡፡

1.የሎሚ ጁስን ብቻውን ወይም ከማር ጋር በመደባለቅ የተጎዳው ፊት ላይ መቀባት እና ለ10 ደቂቃ ቆይቶ በንፁህ ውሃ መታጠብ

2.የጉሎ ዘይት መቀባት

3.የፈረንጅ ዱባን መቀባት እና ለ30 ደቂቃ ያህል ቆይቶ መታጠብ

4.የተፈጨ አጃን ከማር ጋር በመደባለቅ መቀባት ለ30 ደቂቃ ቆይቶ በሞቀ ውሃ መታጠብ

5.የተፈጨ ፓፓያ ከ2 የሻይ ማንኪያ ማር ጋር በመደባለቅ መቀባት እና ለ30 ደቂቃ ያህል ቆይቶ መታጠብ

6.የሽንኩርት ጁስ እና Apple cider vinegar በመደባለቅ መቀባት ለ30 ደቂቃ ያህል ቆይቶ መታጠብ

7.የካካዎ ቅቤ(cocoa Butter) መቀባት

8.ማር እና የተፈጨ ለውዝ በመደባለቅ መቀባት ለ10 ደቂቃ ቆይቶ በሞቀ ውሃ መታጠብ

9.አቮካዶ እና 2 የሻይ ማንኪያ ማር በመደባለቅ መቀባት

10.ኮምጣጤ እና ውሃ እኩል በመመጠን በመደባለቅ መቀባት እና ለ5 ደቂቃ ያህል ቆይቶ መታጠብ

የእናቱን ጉስቁልና ማየት የማይፈልግ ሼር ያድርግ፡፡
—————————

ምንጭ – ዶክተር አለ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *