ስኬታማ ለመሆን ከፈለግክ አንድ ሕግ አክብር፤ፈጽሞ ራስህን አትዋሽ፡፡


ስኬታማ ለመሆን ከፈለግክ አንድ ሕግ አክብር፤ ፈጽሞ ራስህን አትዋሽ፡፡

ህልምህ እንዳይሳካ የሚያደርግ አንድ መጥፎ ነገር አለ እሱም አይሳካልኝም የሚል ፍርሃት።

መከራህ ወደ ስኬት ጫፍ የሚያወጣህ መሰላል ነውና በድል አጠናቀው፡፡

ወደ ስኬት ጎዳና ስትሄድ ስኬትህ ጠላት ሊያፈራብህ እንደሚችል አተዘንጋ፤ ምክንያቱም አብዛኞቹ ስኬታማ ሰዎች ጠላት አላቸውና።

ስኬታማ እንድትሆን ሳይሆን ዋጋ እንዲኖርህ ሻት።

አንድን ነገር ይሳካል ብላችሁ ብዙ ሞክራችሁ ካልተሳካ የሙጢኝ አትበሉ። ምክንያቱም አንዳንዴ በመተው የተሻለ ነገር ይመጣልና፡፡

ስለ ስራህ እድገት አስተያየት የሚሰጥ ወይም የሚተችህ ከሌለ ለስኬት አትበቃም። ስለዚህ ትችትም ሆነ ገንቢ አስተያየትን አትጥላ።

ስኬታማ ሰዎች ከንፈር ላይ ሁለት ነገር ይስተዋላል። አንደኛው «ዝምታ» ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ «ፈገግታ» ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *