በፅሁፍ የቀረበ ……ቡናን ኣብዝቶ መጠቀም የሚያመጣው ችግር

ካፌይን አዕምሮን ለማነቃቃት የሚረዳና በተለይ በቡና፣በሻይ እና በተለያዩ የለስላሳ መጠጦች ውስጥ በስፋት የሚገኝ ኬሚካል ነው፡፡ካፌይን ከእነዚህ መጠጦች በተጨማሪ በቸኮሌቶች ፣በብስኩቶች እና በተለያዩ የህመም ማስታገሻና የራስ ምታት መድሀኒቶች ውስጥ ይገኛል፡፡ይህ ኬሚካል ሱስ የማስያዝ ባህሪው ከፍተኛ ነው፡፡

እነዚህ መጠጦችና ምግቦችእንዲሁም መድሀኒቶች ካፌይን የመያዝ አቅማቸው እንደየሁኔታው የተለያ ሲሆን በቡና ውስጥ የሚገኘው የካፌይን መጠን ግን ከፍ ያለ ነው፡፡

ይህም አንድ ሲኒ ቡና ከ100-150 ሚ.ግ ካፌይን በውስጡ ይይዛል ፡፡
ልላው አንድ ሰው በቀን በአማካይ 80 ሚ.ግ ካፌይን እንደሚወስድ ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡

ታዲያ ከመጠን ያለፈ ካፌይንን መጠቀም ለከፋ የጤና ችግር ያዳርጋል፡፡በካፌይን ሳቢያ ከሚከሰቱ የጤና ችግሮች መካከል የሚከተሉት ተጠቃሽ ናቸው፡፡
፦የእንቅልፍ ማጣት
፦ጭንቀት
፦ራስ ምታት
፦ድብርት
፦ማቅለሽለሽና ማስመለስ
፦የልብ ትርታ መዛባት
የካፌይን መጠኑ እየጨመረ ከሄደ እና 1000ሚ.ግ ከደረሰ የአፍ መኮላተፍ እና ድንገተኛ የልብ ምት መቆም ሊያስከትል ይችላል፡፡

ለእነዚህ በሽታዎች እንዳንጋለጥ ደግሞ ማድረግ ያለብን ተግባራቶች ያሉ ሲሆን እነሱም የምንወስደውን የካፌይን መጠን መቀነስ ፣ካፌይን የሌለባቸውን ምግቦችና መጠጦች ለይቶ በማወቅ መጠቀም፣ ራስን በሌሎች ነገሮች ለማዝናናት መሞከር እና ውሀን አብዝቶ መጠጣት በካፌይን ሳቢያ የሚከሰቱትን የጤና ችግሮች ለማስወገድ ይረዳል፡፡

ሼር ያድርጉ ጤና ይስጥልን
source http://www.gojofilm.com

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *