ዘወትር ማለዳ የምናዘወትራቸውና ለውፍረት ሊዳርጉ የሚችሉ 5 ልማዶች

አዲስ አበባ፣ ህዳር 6፣ 2010 ዘወትር ማለዳ የምናዘወትራቸውና ለውፍረት ሊዳርጉ የሚችሉ 5 ልማዶችን ባለሙያዎች ይፋ አድርገዋል።

የስነ ምግብ እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተመራማሪ የሆኑት ካትሌን አሌውም በማለዳ ከመጠን በላይ እንቅልፍ መተኛት፣ ቁርስ አለመብላት እና ስልክ መነካካት መጥፎ ልማዶች ናቸው ብለዋል።

ካትሌን በማለዳ ቁርስ መብላት እና የአካል ብቃት እንቅሰቃሴ ማድረግ ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል።

ሰዎች በጧት ተነስተው ለጤናቸው ፋይዳ ያላቸውን የአካል እንቅስቃሴዎች ሊያከናውኑ ይገባል ይላሉ።

ሆኖም አንዳንድ ጊዜ በማለዳችን ውስጥ የምናደርጋቸው ጥቂት ልማዶች ከመጠን በላይ ለሆነ ውፍረትና ክብደት ሊያጋልጡን እንደሚችሉ ጥናቶች ይጠቁማሉ።

ከእነዚህም መካከል በስነምግብ እና በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ባለሙያ ካትሌን የቀረቡትና ለውፍረት ሊዳርጉ የሚችሉ አምስት የማለዳ መጥፎ ልማዶች የሚከተሉት ናቸው።

1. ቁርሰ አለመብላት

ቁርስ ሳይበሉ መዋል ሰውነታችን ጤናማ ላልሆኑ ችግሮች እንዲጋለጡና በቀን ውስጥ የሚያስፈልግንን የምግብ ዓይነት እንዳንጠቀም የማድረግ ጫና አለው ነው የተባለው።

በመሆኑም ማለዳ ላይ ከቤተሰብ ጋር ሆኖ ተስማሚ ቁርስ መመገብ ለጤናችን ተስማሚ ከመሆኑም በላይ ቀኑን ሙሉ አዕምሯችን እና አካላችን ደስተኛ እንደሚሆን ተነግሯል።

ቁርስ መመገብ የመራብ ስሜትን፣ ትኩረትን እና ምግብ የመብላት ፍላጎትን እንደሚያሻሽል የስነምግብ ባለሙያዋ ተናግረዋል።

ሆኖም ቁርስ ሳይመገቡ መዋል የአመጋገብ ስርዓትን በማዛባት ሰውነታችን ያልተገባ ምግብ እንዲጠቀም እና ለውፍርት እንዲጋለጥ ሊያደርግ ይችላል ብለዋል።

2. ብዙ ቡና ጠጥቶ በቂ ውሃ አለመጠጣት

ካትሌን በማለዳ ሰዓት ብዙ መጥን ያለው ቡና መመጣት እንዲሁም የምንወስደው ውሃ አነስተኛ ከሆነ ቦርጭ ለማውጣት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው ነው ያስጠነቀቁት።

ውሃ በአካላችን ላይ የሚኖረውን የስብ ክምችት ለማሟት፣ አዕምሯችን ፈጣን እንዲሆን እና ሰውነታችን መርዛማ ነገሮችን እንዲያስወግድ ያግዛል።

ተመራማሪዎች በጠዋት በቂ ንፅህ ውሃ መጠጣት የሰውነት ክብደትን ለመቀነስ እና በእንቅልፍ ወቅት የተከማቹ ውፍረት ፈጣሪ ንጥረ ነገሮችን የማሟት ፋይዳ እንዳለው ይስማማሉ።

3. ከመጠን በላይ መተኛት

ከመጠን በላይ ለሆነ ጊዜ በእንቅልፍ በተለይም ማለዳ ላይ መተኛት የምግብ ምርጫችን ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ የሚያሳርፍ ሲሆን፥ ለውፍረት እንደሚዳርግም ምክንያት ይሆናል።

በተለይም አርፍደን ከእንቅልፍ በምንነሳበት ጊዜ ውፍረትን የሚያመጡ ፈጣን ምግቦችን አዘጋጅተን ልንጠቀም እንችላለን፤ ይህ ደግሞ ጉዳት ነው ይላሉ ተመራማሪዎች።

ከመጠን በላይ እንቅልፍ መተኛት በርካታ የጤና ጉዳቶች ያሉት ሲሆን፥ ከዚህ ውስጥ ደማችን የስኳር መጠን መዋዥቅ እንዲፈጠርበት ሊያደርግ ይችላል ነው የተባለው።

4. ስልክችንን በመናናካት ማሳለፍ

በአልጋችን ላይ እያለን ወይም ከእንቅልፍችን በአግባቡ ሳንነቃ ጀምሮ ጠዋት ጠዋት ስልክ በመነከካት ብዙ ጊዜ የምናሳልፍ ከሆነ ጉዳቱ የከፋ መሆኑ ተነግሯል።

ይህም አዕምሯችን በንፀህ መንፈስ ከመነቃቃት ይልቅ በድብርት እና በቀውስ ውስጥ እንዲያሳልፍ እና የሰውነታችን ክፍሎች ተግባራት እንዲስተጓጎሉ የማድረግ አቅም እንዳለውም ተጠቁሟል።

በተለይም በማህበራዊ የትስስር ገፆች የሚለቀቁ መረጃዎችን እና ምስሎችን የሚመለከቱ ከሆነ አጉል ተስፋ ወይም መጥፎ ስሜት ሊፈጥር ይችላል ነው የተባለው።

5.የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አለማድረግ

ሰዎች ክብደታቸውን ለመቀነስ ጉልበት የሚጠይቁ ስራዎችን በማለዳ እየተነሱ ቢያከናውኑ ይመረጣል።

ሆኖም በተቃራኒው ምንም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ሳያደርጉ ተኝቶ ማሳለፍ ተገቢ አይደለም።

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ የምግብ እና የፍላጎት ተዛምዶን የሚፈጥር ሲሆን ተገቢ ያልሆነ ውፍረትን ለመቀነስም እድል ይፈጥራል።

 

 

 

 

ምንጭ፦www.dailymail.co.uk

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *