የትርፍ አንጀት በሽታ ምልክቶች

የትርፍ አንጀት በሽታ ምልክቶች

• የማያቋርጥና እየጨመረ የሚሄድ የሆድ ሕመም

• ሕመሙ በመጀመሪያ እምብርት አካባቢ ይጀምርና ወዲያውኑ ወደ ታችኛው ቀኝ የሆድ ክፍል ይዞራል፡፡

• መጠነኛ ትኩሳት፣ የሆድ ድርቀት፣ ተውከት ይኖራል፤ የምግብ ፍላጎትም ይቀንሳል፡፡

• የትርፍ አንጀት በሽታን ለማወቅ የሚደረግ ምርመራ
• የሕመምተኛው ሆድ በስተግራ በኩል ከብሽሽቱ በላይ በዝግታ ጠንከር አድርጎ እስኪያመው ጫን ማለትና ከዚያም እጅን በፍጥነት ማንሳት፡፡

• እጅ በሚነሳበት ጊዜ እንደጦር የሚወጋ ሕመም ከተሰማው የትርፍ አንጀት ሕመም መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ በስተግራ በኩል ምንም ዓይነት ሕመም ካልተሰማው በስተቀኝ በኩል በድጋሚ መሞከር ይገባል፡፡

የትርፍ አንጀት መሆኑ ጥርጣሬ ከገባን

• በአስቸኳይ የቀዶ ጥገና ሕክምና ሊያገኝ ወደሚችልበት ሆስፒታል መላክ

• የሚበላም ሆነ የሚጠጣ ነገር መሰጠት የለበትም፤ ሆዱንም ማጠብ አይገባም፤ በሽተኛው ከሰውነቱ ብዙ ፈሳሽ ወጥቶ ድካም ከተሰማው ጥቂት ውኃ ወይም ስኳርና ጨው የተቀላቀለበት ፈሳሽ ፉት እንዲል በማድረግ መርዳት ተገቢ ነው፡፡

• ግለሰቡ ከትከሻው በግማሽ ቀና ብሎ እንዲቀመጥ ማድረግ ለሕመምተኛው ምቾትን ሊሰጥ ይችላል፡፡
source Sci-tech ሳይቴክ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *