ጥብስ ቅጠል አስገራሚ የጤና በረከቶች……..ይሄን ካነበቡ በኋላ አመለካከትዎ ይቀየራል ✔አሁኑኑ ሼር ያድርጉት…


ይሄን ካነበቡ በኋላ አመለካከትዎ ይቀየራል

✔ የማስታወስ ችሎታን ይጨምራል

ከጥንት ጀምሮ ስለዚህ ጥቅሙ የሚነገርለት የጥብስ ቅጠል በውስጡ የያዘዉ ካርኖሲክ አሲድ የአንጎል ነርቮችን የመጠበቅ አቅም ስላለው በህመም ወይም ከእድሜ ጋር በተያያዘ ምክንያት ለሚመጣ የመርሳት ችግር እንዳንጋለጥ ይረዳል፡፡

✔ የማይግሬን ህመምን ያስታግሳል

የጥብስ ቅጠልን በሞቀ ውሃ ዉስጥ በመጨመር ለ 10 ደቂቃ መታጠን ማይግሬን ህመምን ያስታግሳል፡፡
✔ የአፍ ጠረንን ለማስወገድ

የጥብስ ቅጠል ተፈጥሮአዊ የሆነ የአፍ ጠረን ማስወገጃ ነዉ። ትንሽ የጥብስ ቅጠልን በሞቀ ዉሃ ዉስጥ አድርጎ መጉመጥመጥ መጥፎ ጠረንን ያስወግዳል።

✔ የቆዳ መሸብሸብን ይከላከላል

የጥብስ ቅጠል በተለያዩ የቆዳ ማለስለሻ ክሬሞች ዉስጥ የሚገባ ሲሆን ቆዳን እንዳየሸበሸብ እና ጤናማ እንዲሆን ይረዳል።

✔ የፀረ ባክቴሪያነት ጥቅም

ጥናቶች እንደሚያሣዩት ከሆነ የጥብስ ቅጠል እንደ ጨጓራ ባክቴሪያ (H. pylori) እና ሌሎችንም ይዋጋል፡፡

✔ በሽታን የመከላከል አቅምን ያዳብራል

የጥብስ ቅጠል በዉስጡ ያለዉ አንቲ ኦክሲደንት፣ አንቲ ኢንፍላማቶሪ እና አንቲ ካርሲኖጄኒክ ንጥረ ነገር የሰዉነታችንን በሽታ የመከላከል አቅምን እንዲዳብር ይረዳል።

✔ ካንሰርን ይከላከላል

ሮዝመሪ(የጥብስ ቅጠል) በውስጡ የያዘው ካርኖሶል የተባለ ንጥረ ነገር ካንሰርን የመከላከል አቅም እንዳለው ጥናቶች ያሳያሉ፡፡

✔የጥብስ ቅጠል እነዚህ ሁሉ ጥቅሞች ቢኖሩትም ነፍሰጡር ሴቶች እና የደም ግፊት ያለባቸው ሰዎች ግን በብዛት እንዲወስዱ አይመከርም።

✔አሁኑኑ ሼር ያድርጉት…

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *