ሩሲያ በሶሪያ ባካሄደችው የአየር ድብደባ ከ50 በላይ ንፁሃን ዜጎች ህይወት አለፈ

ሩሲያ አየር ሀይል በሶሪያ በፈፀመው የአየር ድብደባ የ53 ንፁሃን ዜጎች ህይወት ማለፉን በአካባቢው ቁጥጥር የሚያደርግ ቡድን አስታወቀ።

የሩሲያ አየር ሀይል የአውሮፕላን ድብደባውን በምስራቃዊ ሶሪያ ገጠራማ አካባቢ በሆነቸው አል ሻፋህ መፈፀሙንም ቡድኑ አስታውቋል።

መቀመጫውን እንግሊዝ ያደረገ የሰብአዊ መብት ተቆጣጠጣሪ ቡድን እንዳስታወቀው፥ ትናንት ጠዋት በተፈፀመው የአየር ድብደባ ከሞቱት ንጹሃን ዜጎች ውስጥ 21 ህጻናት ናቸው።

ዴር አልዞውር አሸባሪው ኢስላሚክ ስቴት (አይ.ኤስ) በሶሪያ የተቆጣጠረው የመጨረሻው ይዞታው መሆኑ ይታወቃል።

መቀመጫውን እንግሊዝ ያደረገው የሰብአዊ መብት ተቆጣጠጣሪ ቡድን፥ በአየር ድብደባው ከሞቱት ውስጥ 34 ሰዎች በመኖሪያ ህንፃዎች ላይ በተፈፀመ ጥቃት መሆኑን አስታውቋል።

የማቾች ቁጥር ከዚህ ከፍ ሊል እንደሚችል ነው የተቆጣጣሪ ቡድኖቹ በመናገር ላይ የሚገኙት።

የአደጋ ጊዜ ሰራተኛ የሆነው ራሚ አብዴል ራህማን፥ “ፍርስራሾችን ማንሳታችንን ተከትሎ የሟቾች ቁጥር እየጨመረ መጥቷል” ብሏል።

ሩሲያ ቀደም ብላ ስድስት የረጅም ርቀት ተጓዠ ቦብም ጣይ አውሮፕላኖች በአካባቢው ላይ ድብደባ በፈፀማቸውን እና ኢላማውም በአካባቢው የሚገኙ የአይ ኤስ ታጣቂዎች መሆኑን አረጋግጣለች።

ሩሲያ የፕሬዚዳንት በሽር አል አሳድ ቁልፍ አጋር ነች።

በተባበሩት መንግስታት ድጋፍ የሚደረግለት የሶሪያ የሰላም ድርድር በቀጣይ ሳምንት እንደሚካሄድ የሚጠበቅ ሲሆን፥ ከዚህ ቀደም በተለያዩ ጊዜያት የተካሄዱ ድርድሮች መክሸፋቸው ይታወሳል።

ምንጭ፦ www.bbc.com and http://www.fanabc.com

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *