ሮበርት ሙጋቤስልጣናቸውን በራሳቸው ፈቃድ ለቀቁ

የዚምባብዌው ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ ስልጣናቸውን በራሳቸው ፈቃድ መልቀቃቸውን የሀገሪቱ ፓርላማ አፈ ጉባኤ ጃኮብ ሙንዴና ተናግረዋል።

ሙጋቤ በፃፉት መልዕክት ውሳኔያቸው በፈቃደኝነታቸው እና ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር እንዲኖር ያደረጉት መሆኑን ገልፀዋል።

አስገራሚው የሙጋቤ ውሳኔ ክስ ተመስርቶባቸው ከስልጣናቸው እንዲነሱ የነበረውን ሂደት እንዲቋረጥ አድርጓል።

ይህ ያልተጠበቀ ውሳኔ የተሰማው የሀገሪቱ ህግ አውጪዎች በሁለቱ ምክር ቤቶች ጥምር ስብሰባ እርሳቸውን ለመክሰስ በሚጠይቀው ሞሽን ላይ እየተወያዩ ባለበት ጊዜ ነው።የሙጋቤን በፈቃደኝነት ከስልጣን መልቀቅ ተከትሎ ዚምባብዌያውያን በመንገዶች ላይ ወጥተው ደስታቸውን እየገለፁ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *