አሜሪካ ለእስራኤል የሚሳኤል መከላከያ የ706 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገች


(ኤፍ.ቢ.ሲ) እስራኤል ለሚሳዔል መከላከያ መርሃ ግብሯ የ706 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ከአሜሪካ ማግኘቷን የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስትር አስታወቁ።

እስራኤል እንደ ሀገር ከተመሰረተች በኋላ ለሚሳዔል መከላከያ ፕሮግራም ያገኘችው ከፍተኛው ድጋፉ እንደሆነ ተጠቁሟል።

የእስራኤል የመከላከያ ሚኒስትር ኢግዶር ላይበርማን በትዊተር ገፃቸው እንድገለፁት በፈረንጆቹ 2018 ለሚሳዔል ፕሮግራም ከፍተኛ ነው የተባለውን የ706 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ደጋፍ የአሜሪካ ኮንገረስ ማፅደቁን ገልፀዋል።

እስራዔልም በዚህ ድጋፍ ዘርፈ ብዙ የሚሳዔል መከላከያ ስርዓትን እንደምትዘረጋም ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

ከዚህም ውስጥም 105 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ድጋፉ ባለፈው ዓመት የተደረገ መሆኑን የገለፁት የአሜሪካ መገናኛ ብዙሀን፥ የ705 ነጥብ 8 ሚሊየን ዶለሩ ድጋፍ በኮንገረሱ መፅደቁን አረጋግጠዋል።

ሚኒስትሩም አሜሪካ ከዚህ በፊት ለእስራኤል አየር ሀይል መከላከያ ያደረገችውን የ6 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ በማስታወስ አሜሪካን አመስግነዋል።

እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ1973 እስከ 2002 1 ነጥብ 6 ትሪሊየን ዶላር ለእስራዔል ድጋፍ ያደረገቸው አሜሪካ በ2016 ለ10 ዓመታት የሚቆይ የ38 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ ማፅደቋም ተገልጿል።

ምንጭ፦ ሚድልኢስት ሞኒተር

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *