አምስት የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ጡረታ ወጡ፡፡


አምስት የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ጡረታ ወጡ፡፡

ጡረታ እንደወጡ ከተጠቀሱት መካከል ጎምቱ የህወሀት መስራችና የውጭ ግንኙነት ስትራቴጂክ ጥናት ኢንስቲትዮት ዋና ዳሬክተር ጄነራል አቶ ስብሃት ነጋ እንደሚገኙበት የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት አስታውቋል፡፡

ፅ/ቤቱ ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለችው ማሻሻያ /ሪፎርም/ የተሳካ እንደሆነ የማድረጉ ስራ እንዲሁም ለህዝብ የልማትና ለውጥ ፍላጎት ተገቢ ምላሽ የመስጠቱ ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሚያግዙ እርምጃዎች እየተወሰዱ እንደሚገኙ ጠቅሷል፡፡ከነዚህ እርምጃዎች መካከል ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ እያካሄዱት ያለው የካቢኔ ለውጥ ይገኝበታል ብሏል፡፡

ዶ/ር አብይ የተለያዩ የመንግስት ተቋማት በአዳዲስ ሀላፊዎች እንዲመሩ እያደረጉ ይገኛሉ ያለው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ከዚህ ስራ ጋር በተያያዘም ለበርካታ አመታት በመንግስት ሀላፊነት ቦታዎች ያገለገሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች በጡረታ እንዳያርፉ እየተደረገ ይገኛል ሲል ተነግሯል፡፡

በጡረታ እንዲያርፉ የተደረጉትም የህወሀት መስራች የነበሩትና የውጭ ግንኙነት ስትራቴጂክ ጥናት ኢንስቲትዮት ዋና ዳሬክተር ጀነራል የሆኑት አቶ ስብሃት ነጋ/አብይ ስብሃትን ጨምሮ አምስት ናቸው፡፡

እነሱም ከፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል ዶክተር ካሱ ኢላላ ፣ ከተቀናጀ የመሬት አጠቃቀም እቅድና ፖሊሲ ዝግጅት ፕሮጀክት አቶ በለጠ ተፈራ ፣ ከንግድና ኢንዱስትሪ የፖሊሱ ዕቅድ አፈፃፀም ክትትል አቶ ታደሰ ሀይሌ እንዲሁም ከፖሊስ ምርምር ማዕከል አቶ መኮንን ማንያዘዋል መሆናቸው ተገልፃል፡፡

ወደፊትም ለረጅም ጊዜ በመንግስት ሀላፊነት እየሰሩ ያሉ ሀላፊዎች በጡረታ እንዲያርፉ የማድረጉ ስራ ይቀጥላል ሲል ጽ/ቤቱ ተናግሯል፡፡

ንጋቱ ሙሉ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *