አትሌት ነጻነት ጉደታ በግማሽ ማራቶን አዲስ ክብረወሰን አስመዘገበች


(ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ነጻነት ጉደታ በ23ኛው የአለም ግማሽ ማራቶን ውድድር አሸናፊ ሆነች።

ትናንት በስፔን ቫሌንሺያ በተካሄደው ውድድር አትሌት ነጻነት በውድድሩ የርቀቱን አዲስ ክብረ ወሰን በማስመዝገብ ነበር አሸናፊ የሆነችው።

21 ኪሎ ሜትሩን ርቀትም 1 ሰዓት ከ6 ደቂቃ ከ11 ሰከንድ በሆነ ጊዜ በመግባት አሸናፊ ስትሆን፥ የርቀቱን ክብረ ወሰንም በ14 ሰከንድ ማሻሻል ችላለች።

የርቀቱ ክብረወሰን ከዚህ በፊት በኬኒያዊቷ ሎርን ኪፕላጋት የተያዘ ነበር።

ክብረ ወሰኑን በማሻሻሏም የ50 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ተሸላሚ ሆናለች።

እርሷን ተከትለው ኬንያውያኑ አትሌቶች፥ ጆስሊን ጄፕኮስጊና ፓውሊን ካቬክ ካሙሉ 2ኛ እና 3ኛ በመሆን ውድድሩን ጨርሰዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *