ከኦሮሚያ እና ኢትዮጵያ ሶማሌ ክልሎች በክልሎቹ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የተመደቡ ነባርና አዲስ ተማሪዎች ምደባ ላይ ለውጥ ተደረገ።

ከኦሮሚያ እና ኢትዮጵያ ሶማሌ ክልሎች በክልሎቹ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የተመደቡ ነባርና አዲስ ተማሪዎች ምደባ ላይ ለውጥ ተደረገ።

ተከስቶ በነበረው የፀጥታ መደፍረስ ምክንያት ተማሪዎች በጊዜያዊነት ወደ ሌሎች የአገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች ተዛውረው ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ መንግስት በወሰነው መሰረት ጊዜያዊ ምደባ መካሄዱን የኢፌዴሪ የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፥ አዲስ ተማሪዎች፣ የሁለተኛ ዓመትና ከዚያ በላይ የሆኑ በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ የኦሮሚያ ክልል ተወላጅ ተማሪዎች እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ሲማሩ የነበሩ እና አዲስ የተመደቡ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ተወላጅ ተማሪዎች በጊዜያዊነት ወደሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች መመደባቸውን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

የ2010 የትምህርት ዘመን አዲስ ተማሪዎቹ ምደባውን በሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ድረገጽ www.app.neaea.gov.et ላይ መመልከት እንደሚችሉ ነው ያመለከቱት።

የሁለተኛ ዓመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ተማሪዎች ደግሞ ጊዜያዊ ምደባው በትምህርት ሚኒስቴር ድረገጽ www.moe.gov.et ላይ እንደሚገኝ በመግለፅ ተማሪዎቹ በጊዜያዊነት ወደ ተመደቡበት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመሄድ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ አሳስቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *