የመሬትን ትክክለኛ ቅርፅ ለማየት ራሳቸውን በሮኬት ያስወነጨፉት አዛውንት


(ኤፍ.ቢ.ሲ) አሜሪካዊ አዛውንት የመሬትን ትክክለኛ ቅርፅ ከላይ አይቶ ለማረጋገጥ በቤታቸው ውስጥ የሰሩት ሮኬት ላይ ሆነው መወንጨፋቸው ተሰምቷል።

ማይክ የተባሉት የ61 ዓመቱ አዛውንት በሰዓት 523 ኪሎ ሜትር በሚፈጥነው ሮኬት ውስጥ በመሆን መሬትን ለቀው 1 ሺህ 875 ጫማ ወደ ሰማይ ተወንጭፈዋል ነው የተባለው።

“መሬት ጠፍጣፋ ነች” ብለው የሚያመምኑት አዛውንቱ፥ ባሳለፍነው ቅዳሜ ነበር በአሜሪካዋ ካሊፎርኒያ አምቦይ ከተባለ በረሃማ ስፍራ የተወነጨፉት ተብሏል።

አዛውንቱ ከከፍታው ላይ ተመልሶ መሬት ላይ ለማረፍም ሮኬቱ ላይ የተገጠመውን ጃንጥላ (ፓራሹት) የተጠቀሙ ቢሆንም፤ ከአደጋ ግን ነፃ መሆን አልቻሉም።

አዛውንቱ አሁን ስላሉበት ሁኔታ ሲያስረዱም፥ ከአስፈሪው አደጋ በኋላ አሁን ላይ ጀርባቸው አካባቢ ከሚሰማው ህመም ውጭ ሙሉ ጤነኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የምድርን ጠፍጣፋነት ለማረጋገጥ ያደረጉት ጉዞም የተሳካ እንደነበረ ነው ማይክ የሚናገሩት።

ማይክ ከዚህ ቀደምም እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2014 ተመሳሳይ ሙከራ በማድረግ ከመሬት 1 ሺህ 374 ጫማ ከፍ ማለት ችለው እንደነበረም ይናገራሉ።

በወቅቱም በደረሰባቸው የመከስከስ አደጋ ለሶስት ቀናት ተኝተው ህክምና ተከታትለው እንደነበረም ተነግሯል።

ምንጭ፦ www.dailymail.co.uk

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *