የአማራና ትግራይ ህዝቦች የምክክር መድረክ ዛሬ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ህዳር 9፣ 2010  በዛሬው ዕለት በጎንደር ከተማ የአማራ እና የትግራይ ክልል እህትማማች ህዝቦች የምክክር መድረክ ይካሄዳል።

የአማራና ትግራይ ህዝቦች የምክክር መድረክ ተሳታፊዎችም ትናንት ጎንደር መግባታቸው ይታወሳል።

መድረኩ የሁለቱን ህዝቦች አንድነት የሚያጠናክር ነው ተብሏል።

ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚቆየው የሰላም ኮንፈረንስ የሁለቱን ክልሎች የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ማጠናከርን መሰረት ያደረገ መሆኑን ተነግሯል።

.jpg

መድረኩ በሁለቱ ክልሎች የሰፈነውን ሰላም ቀጣይነት የማረጋገጥ ዓላማ ያለው ሲሆን፥ ከሁለቱም ክልሎች የተውጣጡ ከ1 ሺህ 300 በላይ የሃገር ሽማግሌዎች፣ ምሁራን እና የህዝብ ተወካዮች ይሳተፉበታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *