የጥቅምት ወር የዋጋ ግሽበት ወደ 12 ነጥብ 2 በመቶ ከፍ አለ

የጥቅምት ወር የዋጋ ግሽበት ወደ 12 ነጥብ 2 በመቶ ከፍ አለ

  የጥቅምት ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 12 ነጥብ 2 በመቶ ሆኖ መመዝገቡን የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ገለፀ።

ኤጀንሲው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ፥ በያዝነው ወር የእህል ዓይነቶች በተለይም የጤፍ፣ የበቆሎ፣ የስንዴና የገብስ ዋጋ በአብዘኛዎቹ የአገሪቱ ክልሎች የመረጋጋት ሁኔታ ታይቷል።

የጤፍ፣ የበቆሎና የስንዴ ዋጋ በአንዳንድ ክልሎች መጠነኛ ቅናሽ አሳይቷል። በጥናቱ ወር የበሬ ሥጋ፣ የቁም በግና ዶሮ፣ ወተት፣ አይብና ዕንቁላል፣ ቅቤና ቀይ ሽንኩርት ዋጋ ላይ መጠነኛ ቅናሽ ታይቷል።

የፍራፍሬ በተለይም ሙዝ፣ ስኳር እና ቡና ዋጋ በጥቅምት ወር ዋጋቸው ጨምሯል።

የቲማቲምና የካሮት ዋጋ ከተጠበቀው በላይ ጭማሪ አሳይቷል።

በአጠቃላይ ካለፈው ወር ጋር ሲነፃጸር በዚህ ወር የእህልና የጥራጥሬ ዋጋ መጠነኛ መረጋጋት የታየበት ቢሆንም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃጸር ግን የዋጋ ግሽበቱ ከፍ ማለቱን ነው ኤጀንሲው ያስታወቀው።

የመስከረም ወር የዋጋ ግሽበት 10 ነጥብ 8 በመቶ ሆኖ መመዝገቡ ይታወሳል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *