የፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን የአዲስ አበባ የላዳ ታክሲ ባለቤቶችንና ሾፌሮችን ሰብስቦ ዛሬ ረፋድ መከራቸው፡፡


የፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን የአዲስ አበባ የላዳ ታክሲ ባለቤቶችንና ሾፌሮችን ሰብስቦ ዛሬ ረፋድ መከራቸው፡፡

በባለስልጣኑ መስሪያ ቤቱ የመንገድ ደህንነት ትምህርትና ግንዛቤ ዳይሬክተሩ አቶ ዮሐንስ ለማ ለሸገር ሲናገሩ ላዳ ታክሲዎች ከመደበኛው የከተማው ትራንስፖርት አገልግሎታቸው ባለፈ በርካታ የውጪ ሀገር ዜጎችን ከኤርፖርት፣ ሆቴል፣ ከቦታ ቦታ የሚያዘዋውሩ በመሆናቸው የሾፌሮቻቸው ሥነ ምግባርና የታክሲዮቹ የቴክኒክ ብቃት የተስተካከለ መሆን ስላለበት ነው ለባለቤቶቻቸውና ለሾፌሮቻቸው ምክር መስጠት ያስፈለገው ብለዋል፡፡

በከተማው የአንዳንድ ላዳ ታክሲ ሾፌሮች መጠጥን በውሃ መያዣ ላስቲኮች በመያዝ፣ ጫት በመቃም በሌሎችም የባህሪ ችግሮች ውስጥ ሆነው መኪኖቹን ማሽከርከራቸው አሮጌና የቴክኒክ እክል የበዛባቸው ላዳዎች መብዛታቸው ለዛሬው የምክር ፕሮግራም መነሻ ሆኗል ሲሉ ለሸገር ተናግረዋል፡፡

ሾፌሮቹ ቀንም ሌሊትም መንዳታቸው ለትራፊክ መንስኤ እየሆነ ነው ተብሏል፡፡
በፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን አዳራሻ ዛሬ ለግማሽ ቀን በተከናወነ ፕሮግራም ላይ 1 ሺ የሚሆኑ የላዳ ባለንብረቶችና ሾፌሮችም የተገኙ ቢሆንም፤ በቂ አይደለም እንዲህ ያለው ምክር ወደፊትም ይሰጣል ብለዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከ7 ሺህ በላይ የላዳ ታክሲዎች አሉ ተብሏል፡፡

(ወንድሙ ኃይሉ)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *