የ68 ዓመቱ ወጣት


(ኤፍ.ቢ.ሲ) ቻይናዊው ሁ ሀይ የ68 ዓመት አዛውንት ሲሆኑ፥ ያላቸው ቁመና ግን ወጣቱ አዛውንት አስብሏቸዋል።

በሻንጋይ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አዛውንቱ በዚህ እድሜያቸው የወጣት ቁመና በመያዛቸው ከበርካቶች አድናቆት እየጎረፈላቸው ሲሆን፥ ከሁለት ዓመት በፊትም ዘመናዊው አያት የሚል ሽልማት አግኝተው ነበር።

እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1950 የተወለዱትን ሁ ሀይን ያየ ሰው እድሜያቸው 68 ዓመት ነው ሲባል ለማለን ይቸገራል ነው የተባለው።

ከልጅነታቸው አንስቶ የተለያዩ ስፖርቶችን መስራትን እንደሚያዘወትሩ የሚናገሩት ሁ ሀይ፥ የወጣት አቋም እንዲኖራቸው የረዳቸው ስፖርቱ እንደሆነ ነው የሚናገሩት።

ከዚህ በተጨማሪም ጤናማ ምግብ ማዘውተር እና የተለያዩ አጋዥ ቫይታሚኖችንም እንደሚወስዱ ነው ወጣቱ አዛውንት ሁ የሚናገሩት።

ከእነዚህ ውጭ ግን የወጣት አቋም እንዲኖራቸው ያደረገው ዋነኛው ሚስጥር ሁሌም ራሳቸውን እንደ ወጣት ማየታቸው እና ውስጣቸው ላይ የወጣት አስተሳሰብ ስላለ ነው።

ሁ ይናገራሉ፥ “ሁሌም የወጣት ቁነማ እንዲኖረኝ ያደረገኝ ራሴን የ20 ዓመት እድሜ ያለው ወጣት አድርጌ ስለማስብ ነው፤ እስከ ህይወቴ ፍፃሜ ድረስም አስተሳሰቤ አይቀየርም” ብለዋል።

“ለእኔ እድሜ ቁጥር ነው” የሚሉት አዛውንቱ ሁ፥ “የወጣትነት ስሜት እስከተሰማኝ ድረስ የእድሜዬ ቁጥር ምንም ተፅእኖ አይፈጥርብኝም” ነው ያሉት።

ምንጭ፦ www.odditycentral.com

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *