ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የህወሓት ሊቀ መንበር ሆነው ተመረጡ

ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የህወሓት ሊቀ መንበር ሆነው ተመረጡ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 20 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ከአንድ ወር በላይ ሲያካሂድ የነበረውን ስር ነቀል ግምገማ ሂስና ግለ ሂስ ህዳር 20 ቀን 2010 በድል ማጠናቀቁን ገለፀ።

ከግምገማው በኋላ በሂስና ግለ ሂስ የማጥራት እርምጃ በመውሰድ፥ ዘጠኝ አባላት ያሉት የድርጅቱን ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫን በዴሞክራሲያዊ አግባብ አካሂዷል።

በዚህም መሰረት፦ ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል

ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር

አቶ ጌታቸው አሰፋ

አቶ አለም ገብረዋህድ

ዶክተር አዲስአለም ባሌማ

አቶ አስመላሽ ወልደስላሴ

አቶ ጌታቸው ረዳ

ወይዘሮ ኬርያ አብርሃም እና

ዶክተር አብርሃም ተከስተ

የህወሓት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ተደርገው ተመርጠዋል።

ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የድርጅቱ ሊቀ መንበር ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረአግዚአብሄር ደግሞ ምክትል ሊቀ መንበር ሆነው መመረጣቸውንም ማዕከላዊ ኮሚቴው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ አስታውቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *