ጠቅላይ ሚኒስተር ዶክተር አብይ አህመድ በሼህ መሐመድ ጉዳይ ከሳዑዲው ንጉስ ጋር ተነጋገሩ


የሳዑዲው ንጉስ ሳልማን ቢን አብዱልአዚዝ አል ሳውድ፣ ዶክተር አብይ አሕመድ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስርት ሆነው በመመረጣቸው የደስታ መልክት አስተላልፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ የደስታ መልክቱን በመቀበል፣ በሁለቱ ሀገሮች መካከል ያለውን ግንኙነት ከፍ ወዳለ ደረጃ ለማድረስ አብረው ለመስራት ዝግጅ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በስልክ ውይይታቸው፣ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ ያላቸው እና የኮርፖሬት ማሕበራዊ ሃላፊነታቸውን ከሚገባው በላይ መወጣት የቻሉትን የሼህ መሐመድ አሊ አልአሙዲን ጉዳይ አንስተው መወያየታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ምንጮች አረጋግጠዋል።

በቅርቡም አንድ የልዑካን ቡድን ወደ ሳዑዲው ዓረቢያ ይጎዛል።

ፈኑኤል ክንፈ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *