ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሰሜን ኮሪያ ጉዳይ ላይ ለመምከር ቻይና ናቸው

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሰሜን ኮሪያ ጉዳይ ላይ ለመምከር ቻይና ናቸው

 አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ቻይና ገብተዋል።

የፕሬዚዳንቱ የቻይና ጉብኝትም ሰሞኑን በእስያ ሀገራት የሚያደርጉት ጉብኝት አካል ነው።

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በደቡብ ኮሪያ ሲያደርጉ የነበረውን ጉብኝት አጠናቀው ነው በዛሬው እለት ቻይና የገቡት።

ቻይና ሲደርሱም የቻይናው ፕሬዚዳንት ዢ ጂምፒንግ ጨምሮ ከፍተኛ የሀገሪቱ ባለስልጣናት ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የጉብኝታቸው ዋነኛ አላማም ሰሜን ኮሪያ የምታደርገውን የኒኩሌር የጦር መሳሪያ ግንባታ ዙሪያ ላይ ለመምከር መሆኑ ተነግሯል።

ፕሬዚዳንቱ ወደ ቻይና ከማቅናታቸው በፊት በጃፓን እና በደቡብ ኮሪያ ጉብኝት አደርገዋል።

በጃፓን ቶኪዮ ቆይታቸውም ከጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ ጋር በሰሜን ኮሪያ፣ በሁለትዮሽ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

ጃፓን በአሜሪካ ሰራሽ የጦር መሳሪያ የፒዮንግያንግን ሚሳኤሎች መምታት ትችላለች የሚል ንግግር ማድርጋቸውም ተገልጿል።

በደቡብ ኮሪያ ባደረጉት ቆይታም በሀገሪቱ ፓርላማ በመቅረብ ንግግር ያደረጉ ሲሆን፥ በንግግራቸውም ሰሜን ኮሪያን ማስቆም በሚቻልበት ላይ ያጠነጠነ ነበር ተብሏል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *