የተኛውን ባሏን እጅ ተጠቅማ ስልኩን በመክፈት ሌላ ሴት እንደደረበባት ያወቀችው ሴት አውሮፕላኑ ያለቦታው እንዲያርፍ አድርጋለች።

የተኛውን ባሏን እጅ ተጠቅማ ስልኩን በመክፈት ሌላ ሴት እንደደረበባት ያወቀችው ሴት አውሮፕላኑ ያለቦታው እንዲያርፍ አድርጋለች።

(ኤፍ ቢ ሲ) በበረራ ወቅት የተኛውን ባሏን የጣት አሻራ ተጠቅማ ስልኩን በመክፈት ሌላ ሴት እንደደረበባት ያወቀችው ሴት አውሮፕላኑ ያለቦታው እንዲያርፍ አድርጋለች።

የኳታር አየር መንገድ ተጓዞቹን አሳፍሮ ከዶሃ ወደ ኢንዶኔዥያዋ ከተማ ባሊ በመጓዝ ላይ ነው።

ከተጓዦች መካከል ኢራናዊት ሴት ከባሏ እና ከልጇ ጋር ቤተሰቡ በአንድ ላይ ይገኙበታል።

በጉዞ መሃልም ባል እንቅልፉን ተኝቶ ነበር፤ በዚህ አጋጣሚም ሚስት የተኛውን ባሏን የእጁን ጣት አሻራ በመጠቀም የተቆለፈውን ስልኩን ትከፍታለች።

በዚህ ጊዜ ስልኩን ስትበረብር ድንገት ልዩ ነገር ታገኛለች፤ ባሏ በእሷ ላይ ሌላ ሴት መደረቡን ወይም መማገጡን የሚያሳዩ የመልዕክት ልውውጦችን ማግኘቷ እጅግ ያስደነግጣታል።

ባገኘችው ነገርም ተበሳጭታ፥ ቧሏን መደብደብ ትጀምራለች።

በአውሮፕላኑ ላይ የተከሰተውን ያልተለመደ የባልና የሚስት ግርግር የሰሙት የበረራ ሰራተኞችም ጣልቃ ገብተው ለማረጋጋት ቢሞክሩም አልተሳካም።

አውሮፕላኑ እየበረረ ቢሆንም ብጥብጡ ግን አሁንም አልቆመም፤ በዚህም ምክንያት አብራሪው ባላሰበው ሁኔታ በድንገት አውሮፕላኑን በህንዷ ከተማ ቼናይ ለማሳረፍ ተገደደ።

ብጥብጥ የፈጠሩት ባልና ሚስት ልጃቸውን ጨምረው ከአውሮፕላኑ እንዲወርዱ ተደረገና በረራው ወደ ኢንዶኔዥያ ተጀመረ።

ከአውሮፕላኑ እንዲወርዱ የተደረጉት ግጭት ፈጣሪ ቤተሰቦች እንዲረጋጉ ተደርጎ በባቲክ አውሮፕላን ወደ ኳላላምፑር እንዲጓዙ ተደርገገዋል።

 

 

 

ምንጭ፦www.nydailynews.com

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *