መነበብና ሼር መደረግ ያለበት ገራሚ ታሪክ


ሁሉም ሰው ሼር. አስተማሪ ስለሆነ

“አንድ 60ሰዎችን የገደለ ወንበዴ ወደ አንድ አባት መጥቶ ንስሃ ስጡኝ 60 ሰው ገድያለው አላቸው እሳቸው አንተማ ሰይጣን ነህ ከኔ ራቅ ቢሉት እሳቸውንም ገደላቸውና ሄደ።
ሌላ ቄስ አገኘ “አባቴ ንስሀ ይስጡኝ 60 ሰው ገድያለው ይህንንም ብዪ የጠየክዋቸው ካህን ሰይጣን ብለውኝ እሳቸውንም ገድያለው “ካህኑም አንተ አረመኔ እኔንም ልትገድለኝ ነውን?
ቢሉት እሳቸውንም ገደላቸው በዚህ ሁኔታ ሌላ ሁለት ካህናትንም ገድሎ ወደ ለመደው ውንብድናው እየሄደ ሳለ
አንድ ሽማግሌ መነኩሴ ውሃ ሊቀዱ እየሄዱ አገኘና አንቱ ሽማግሌ ይቁሙ አላቸው። “አቤት ልጄ” አሉት ” 60 ሰዎቹን
ገድዪ ንስሃ ልገባ ብጠይቅ አልፈቅድ ብለውኝ 4 ካህናትን ገድያለሁ እርሶንም ንስሃ ማይሰጡኝ ከሆነ እገድሎታለው “አላቸው
እሳቸውም ስቅስቅ ብለው አለቀሱለት “በእውነት እግዚአብሄርን በድለሃል አስከፍተሀል እርሱ ግና መሃሪ አምላክ
ነው” አሉት፡፡
ከዛም ወደ ጉድጉዋድ ወሰዱትና “ላንተ እጸልይልህ ዘንድ የጸሎት መጸሃፌ እዚ ወድቆዋልና አውጣልኝ “አሉት
ከዛ ወደ ጥልቁ በገመድ አንጠልጥለው አስገቡት መግባቱን ሲያረጋግጡ ገመዱን ቆረጡ ወንበዴውም አንተ ሽማግሌ
እገድልሃለው እያለ መዛት ጀመረ ትተውት ሄዱ።
ከ 9 ሰአት በውሃል ቂጣ እና ውሃ ይዘው መጥተው “ልጄ እንዴት ነህ “አሉት እገድልሀለው አለ ምግቡን ሰጥተውት
ሄዱ፡፡
ከ12 ሰአት በውሃላ ተመለሱ “ልጄ እንደምን አለህ ” ደከም ባለ ድምጽ እገድልሀለው አለቅህም ምግብ ሰጥተውት
ሄዱ፡፡
አንድ ቀን ቆይተው መጡ “ልጄ እንደምን አለህ ” ሲሉት “እ..ገ..ድል..ሀለው” አለ እጅግ በደከመ ድምጽ ምግቡን
ሰጥተውት ሄዱ፡፡
አሁንም አንድ ቀን ቆይተው ተመለሱና “ልጄ
እንደምን ዋልክ” ሲሉት
“””ፈጣሪ ይመስገን””” አለ ትዕቢቱ በጾም ተሸነፈ፡፡
ነብስ ስጋን አሸነፈች እሳቸውም በገመድ አውጥተው ንስሃን ሰጡት ከዚያ በኋላ የአምላክ ባርያ ሆኖም ኖረ፡፡”
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡ ~ ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ሁላችንንም ፈጣሪ አምላክ በቸርነቱ ፡ በምህረቱ ይጠብቀን !!!
ለንስሀ ሞት ለአክብሮት-ሠንበት ያብቃን፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡~ ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡ አሜን!!!

ሼር ያድርጉት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *