በኢትዮጵያ ፓስፖርት ካለ ቪዛ ሊጓዙባቸው የምችሉባችው 10 ሃገራት

በኢትዮጵያ ፓስፖርት ካለ ቪዛ ሊጓዙባቸው የምችሉባችው 10 ሃገራት

ኢትዮጰያውያን በ37 ሃገራት ካለ ቪዣ እና በደረሱባቸው ሃገራት ቪዛቸውን ማግኘት የሚችሉ ሲሆን ይሄ ደግሞ የኢትዮጵያን ፓስፖርት በቪዛ ሪስትሪክሽን ኢንዴክስ መሰረት ከአለም በ98ኛ ደረጃ ያስቀምጣታል። ቀጥለን የምናያቸው 10 ሃገራት ኢትዮጵያውያን ካለ ቪዛ በቀጥታ ፓስፖርታቸውን ብቻ በመያዝ  ሊገቡባቸቀው የሚችሉባቸው ሲሆኑ አንዳንዶቹ ደግሞ E-VISA (ኤሌክትሮኒክ ቪዛ )በመያዝ መግባት ይችላሉ።

10) ኬኒያ፦ ኢትዮጵያውያን ካለ ቪዛ ወደ ጎረቤት ሃገር ኬኒያ  መግባት የሚችሉ ሲሆን ከሶስት ወር በላይ የሚቆዩ ከሆነ ግን ቪዛ የመያዝ ግዴታ ይኖርቦታል።

9)  ጋቦን፦ ወደ ምእራባዊቷ አፍሪካ ጋቦን መሄድ የሚፈልጉ ከሆነ ፓስፖርትዎን እና  ከonline ላይ ኤሌክትሮኒክ ቪዛ ፕሪንት በማድረግ ከያዙ ወደ ጋቦን መግባት ይችላሉ።

8) ዶሚንክ ፦ በካሪቢያን ደሴቶች ወደ ምትገኘው ዶሚኒክ ለጉብኝት መጓዝ ከፈለጉ እስከ 21 ቀናት ካለ ቪዛ መቆየ ይችላሉ።

7) ማይከሮኔዢያ ፦ የአሜሪካ ተዛማጅ ወደሆነችው ማይክሮኔዢያ መጓዝ ከፈለጉ ለ30 ቀናት ካለ ቪዛ መቆየት ይችላሉ።

6) ሴንት ቬንሰንት፦ ወደ ደቡብ አሜሪካ ወደ ምትገኘው ሴንትቨንሰንት ለ1ወር ያህል ካለ ቪዛ ተጉዘው ጎብኝተው መመለስ ይችላሉ።

5)  ፊሊፒንስ፦ ኢትዮጵያውያኖች ወደ ፊሊፒንስ መጓዝ ከፈለጉ ለ30 ቀናት ካለቪዛ በፊሊፒንስ መቆየት ይችላሉ።

4) ሲንጋፖር፦ የአለም የኮሜርስ እና የፋይናንስ ማእከል ወደ ሆነችው ሲንጋፖር መጒዝ ከፈለጉ ለአንድ ወር ካለ ቪዛ መጓዝ እና መቆየት ይችላሉ

3) ሄይቲ ፦ ከቅርብ አመታት በፊት በመሬት መንቀጥቀጥ  ብዙ አደጋ የደረሰባት ሄይቲ  ኢትዮጵያውያኖችን ለሶስት ወራት ያክል ካለ ቪዛ ለመቀበል እና ለሞቆየት ትፈቅዳለች።

2) ጆርጂያ፦ በዩሮ ኤዢያ ወደ ምትገኘው ጆርጂያ መጓዝ ለሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን ከኦንላይን ኤሌክትሮኒክስ ቪዛ ፕሪንት አድርጎ በመያዝ ብቻ ወደ ጆርጂያ መግባት ይችላሉ።

1)  አውስትራሊያ፦ ወደ አውስትራሊያ ለጉብኝት መጒዝ ለሚፈልጉ ኢትዮጵያውያኖች ከኦንላይን የE600 ቪዛ ኦርደር በማድረግ ወደ አውስትራሊያ መጓዝ ይችላሉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *