ቱርካዊው የዓለማችን ባለረጅም አፍንጫ

ቱርካዊው መሀመት ኦዝዩርክ የዓለማችን የረጀም አፍንጫ ባለቤት ነው።

8 ነጥብ 8 ሴንቲ ሜትር (3 ነጥብ 46 ኢንች) በሚረዝመው አፍንጫው ነው መሀመት ኦዝዩርክን የረጅም አፍንጫ ባለቤት ያደረገው።

የመህመት አፍንጫ የተለካው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2010 በጣሊያን ሮም ከተማ ሲሆን፥ በወቅቱም በቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት ተላልፎ እንደነበረም ይታወሳል።

መህመት በችኛው የዓለማችን የረጅም አፍንጫ ባለቤት አይደለም የሚሉ መረጃዎችም በወቅቱ ተያይዘው ነበር።

እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1970 እንግሊዛዊው የሰርከስ ተጫዋች ቶማስ ዌደርስ 19 ሴንቲ ሜትር (7 ነጥብ 5 ኢንች)የሚረዝም አፍንጫ ነበረው ተብሏል።

ምንጭ፦ Guinness World Records

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *