አስደሳች ዜና – አፀደ ንጉሴ በዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታልም የዓይን ልገሳ አግኝታለች


እህታችን አፀደ ንጉሴ ታይላንድ ሃገር ሄዳ የመጀመርያ ህክምና ብታደርግም ብዙም ለውጥ ሳይኖራት ወደ ሃገር ቤት ተመልሳለች፡፡

አዲስ አበባ ውስጥ ማረፍያና የሚረዳት ሰው ባለመኖሩ በከፍተኛ ወጪ ሆቴል እየከፈለች እንዲሁም የተወሰነ ጊዜም አንድ የተባረከ ሰው እያኖራት ነበረ፡፡

ነገር ግን የአዲስ አበባ ሴቶች ማህበር በደረሰው ጥቆማ መሰረት የማህበሩ አመራሮች አፀደን በመጎብኘት ያዩት ነገር እጅግ ልብ የሚነካ በመሆኑ አፋጣኝ እርምጃ በመውሰድ የመጠልያ የምግብ የህክምና እና የሕግ አገልግሎት እንድታገኝ ማድረግ ጀመሩ፡፡

በተለይ በተለይ ኤሜሪካ ውስጥ ታዋቂ ሰዎች የፕላስቲክ ሰርጀሪ በመስራት የሚታወቀው ዶ/ር ቴዎድሮስ አይኮን የህክምና ማዕከል ማህበሩ ከፍተኛ ወጪ በማውጣት ተከታታይ ህክምና እንድታገኝ ማድረግ ተያያዘ፡፡

ከነበረችበት ተጨባጭ ለውጥ እያመጣች ሄደ፡፡

ይህ በእንዲህ እያለ ማህበሩ የተሻለ ህክምና እንድታገኝ በደራው ጨዋታ የሬዲ ዝግጅት በጋዜጠኞቹ፤ ደረጀ ሀይሌ እና በአርቲስት አዜብ ወርቁ አዘጋጅነት አሜሪካን ሃገር ሄዳ ህክምና እንድታገኝ ጥረት ቀጥሏል፡፡

ማህበሩ ሙሉ ወጪዋ እየተሸፈነ ተከታታይ ቀዶ ጥገና እየተደረገላት ይገኛል፡፡
በዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታልም የዓይን ልገሳ በማድረግ ማየት ትችል ዘንድ ከፍተኛ ህክምና እንድታገኝ የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ማህበር አመቻችቷል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ማህበር ለሴቶች የቆመ ህዝባዊ ማህበር እንደ መሆኑ መጠን እህታችን አፀደ የተሻለ ህይወት እንዲኖራት ከፍተኛ ድጋፍ እና ክትትል እንደሚያደርግ ቃል ገብተዋል፡፡

በዚህ አጋጣሚ ማህበሩ ላደረገው እና አሁንም ለሚያደርገው ሁሉ በሰሟ ቤተሰቦችዋና አፀደን ለማገዝ የተቻለውን ሁሉ ባደረጋቹ ወገኖች ስም ምስጋናችን ለአዲስ አበባ ሴቶች ማህበር ይድረስልን፡፡

Thank u.
ሂሳብ ቁጥር
አፀደ ንጉሴ አብርሃ 1000138577841
ፀጋ ንጉሴ አብርሃ 1000077189018
ተጨማሪ መረጃ
FB – Sami Amare +251-910-477237

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *