አትላንታ ኦሎምፒክ ጀግናው ኃይሌ ገብረሥላሴ በ10ሺ ወርቅ የወሰደበት .. ጀግናዋ ፋጡማ ሮባም በማራቶን ድል የተቀዳጀችበት ዶም ነገ በድማሚት ሊፈርስ ነው

Bye Bye GA dome ጆርጂያ ዶም – ቻዎ!

Built in 1992, it was the largest covered stadium with a capacity of holding 71,000 attendees. The cost to build this Stadium was 214 millions dollars.It took 4 years to complete

ጆርጂያ ዶም የተሰኘው ስቴዲየም በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1992 ዓ.ም በ214 ሚሊዮን ዶላር ነው የተገነባው። 71ሺ ሰው ይይዛል። ዝግ ስቴዲየም ሆኖ ይህን ያህል ሰው በመያዝ በዓለም ደረጃም ስሙ ይነሳል። አሁን ግን ሌላ ስቴዲየም፣ በቅርብ ርቀት (80ሺ ሰው የሚይዝ) በመሰራቱ፣ ይህኛው እንዲፈርስ ተወስኖበታል። እናም ነገ ሰኞ ጠዋት 20 ሰከንድ ብቻ በሚፈጅ ማፈራረሻ ድማሚት ይፈርሳል። ከዚህ በፊት የኢትዮጵያውያን ስፖርት በዓልም በዚህ ስቴዲየም ተደርጎ እንደነበር ይታወሳል። ትላልቅ የ እንግሊዝ ፕሪሚየር ቡድኖችም እየመጡ የወዳጅነት ጨዋታዎች አድርገውበታል። አትላንታ ኦሎምፒክም እዚሁ ነው የተደረገው::

በ1996ቱ አትላንታ ኦሎምፒክ ጀግናው ኃይሌ ገብረሥላሴ ወርቅ በ10ሺ ወርቅ የወሰደው እዚሁ ዶም ነበር .. ጀግናዋ ፋጡማ ሮባም በማራቶን ስታሸንፍ ቁጭ ብድግ ያሰኘችን የመጨረሻዎቹን ደቂቃዎች እዚሁ ስቴዲዮም ውስጥ ሮጣ ነበር።

ለማንኛውም ሰኞ ጠዋት 7 ሰአት አካባቢ ወደ ዶሙ አካባቢ ያሉ መንገዶች ሁሉ ይዘጋሉ። ቻናል 2 ቲቪ ደግሞ ሲፈርስ በቀጥታ አስተላልፋለሁ ብሏል።

GA dome, hosted Olympic, [where hour hero Haile G. Sellasie took Gold in this dome] English premier Clubs friendly games, and also hosted the 2004 Ethiopian Soccer Festival. Now this stadium is going to be implode with an explosive. Since the new stadium, another Dome, is built across the road, this one will be gone forever.

So, the DATE IS tomorrow, Monday, Nov. 20. at 7am . All roads to the area will be closed. Channel 2 TV will broadcast the implosion live. Authorities said, it will only take 20 Seconds to demolish it. በጆርጂያ ዶም ትዝታ ያላችሁ – ቻዎ በሉት !

ሆነም ቀረ .. ዓመታት የሚወስደው መስራት እንጂ ማፍረስ እንዲህ የ20 ሰከንድ ነገር ነውና ፣ አንድን ነገር፣ ታሪካችንን፣ ወጋችንን፣ ባህላችንን፣ ማንነታችንን ለማፍረስ አንቸኩል። መስራት እንደማፍረስ ቀላል አይደለም።
_______
[እንዳለ በሆነ ቴክኖሎጂ ከሥሩ ነቅሎ ወዳገራችን መውሰድ ቢቻል እንዴት ነው? .. ለነገሩ አሁን አሁን አገራችን መሄዱ ሳይሆን ሄዶ የት ቦታ ይሁን የሚለው ሊያጣላን ስለሚችል …. እኛ ስንጣላ ፈረንጆቹ ሃሳባቸውን ቀይረው ኬንያ ሊወስዱት ይችላሉ]

ምንጭ አድማስ ሬዲዮ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *