ኢትዮጵያዊው ታክሲ ሾፌር በጥይት ተመታ

ኢትዮጵያዊው ታክሲ ሾፌር በጥይት ተመታ Ethiopian taxi driver shot !!

The driver, Alem, is recovering in hospital with a wounded shoulder and police are still hunting for the man who fired the gun and the woman who was with him. This happened Yesterday, Nov. 19 in New Zealand City of Wellington.

ነገሩ የሆነው በሚጢጢዋ ደሴት ኒውዚላንድ ነው። በዋና ከተማዋ ዌሊንግተን፣ አገር ሰላም ብሎ አለም የተባለ ታክሲ ሾፌር፣ እየሾፈረ ነበር። መንገድ ላይ አንድ ወንድና አንዲት ሴትን ይጭናል። አድርሰን ያሉት ቦታም ያደርሳቸዋል። አለም ለከተማው ጋዜጣ ሲናገር፣ “ከደረሱ በኋላ ሳይከፍሉ ወረዱ፣ ምንም አላልኳቸውም፣ ወዲያው ሰውየው ከኪሱ ሽጉጥ አውጥቶ ተኮሰብኝ፣ ወዲያው አስነስቼ በፍጥነት ሄድኩ፣ እጄ ላይ ነው የተመታሁት፣ ብዙም ደም እየፈሰሰኝ ነበር፣ ክፍሉ አላልኳቸውም ፣ ለገንዘቡ ግድም አልነበረኝ፣ ለምን እንደተኮሱ ግን ግራ ገብቶኛል” ነበር ያለው።

Alem, who is from Ethiopia, said there was no argument over the fare – the couple got out of his car without paying, which he said “didn’t care”

The man for no reason, then pulled out a pistol, told Alem to get out the car and when he refused, shot him. Alem said he took off in his car terrified the man was about to fire again and kill him. He got help at a nearby petrol station. NewZealand is a tiny Island in the Pacific which population is around 4 million.

ተኳሹ እንደገና ሊተኩስ ሲል እንዳመለጠ የሚናገረው አለም፣ ለህይወቱ አስጊ ሁኔታ እንደነበር ገልጾ፣ የማያውቃቸው ሰዎች ተባብረውት ሆስፒታል መድረሱን አክሎ ገልጧል። ፖሊስ ታክሲ ውስጥ የነበረውን ካሜራ እያጠና እንደሆነም ተገልጧል።

በፓስፊክ ውቂያኖስ ላይ የምትገኘው ትንሽቷ አገር ኒውዚላንድ ከ4 ሚሊዮን የማይበልጡ ነዋሪዎች ያሏት ደሴት ነች።

source አድማስ ሬዲዮ Admas Radio

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *