#እውነተኛ___ታሪክ____ rip


#እውነተኛ___ታሪክ____ rip
ከእለታት አንድ ቀን ልጅና አባት በፍቅር፣በደስታ በተሞላበት ቤት አብርው ይኖራሉ። ውዴታቸው መችም ከሌሎች የተለየ ነበር ምክንያቱም አንዱ ካንዳቸው ተነጥለው መኖር የሚችሉ አይመስል ። ከለታት አንድ ቀን ልጅ ትታመማለች አባት ልጁን ይዞ ሀኪም ቤት ሄደ።
ሀኪም መፍትሄ አልሰጣትም ልጅት አሁንም አልተሻላትም
ልጁን ይዞ ወደ ፀበል ወሰዳት መፍትሄ የለም የሳይኮ ሎጅ ባለሙያ አማከራ፣ያልሄደበት የለም በቃ,,,,,,,,,,,
ልጅት ግን ልትተርፍ አልቻለችም ልጁ ሞተች ። አባት አንጀቱ ተቆርጠ፣የሚይዘው ፣የሚጨብጠው አጣ ተስፋ ቆርጦ ቤት ዘግቶ እራሱን በሀዘን መቅጣት ጀመር። ሌት ተቀን ማልቀስ ማልቀስ በእንባ ሲታጠብ ይውላል፣ያድራል።
የሰፈሩ ሰወች ሊያፅናኑ፣ሊያበርታቱ ቢሞክሩም እሽ አላለም ባሰበት ሀዘኑ ።

አንድ ቀን በህልሙ ሰማይ ላይ ያሉ ህፃናት ልጆች ውድድር ይቀርባሉ ለሁሎች ሻማ፣ጧፍ ተሰጡ እና አሁን ሁላችሁም አብሩት ተባሉ ሁሉም አበሩት።ነገር ግን የሱ ልጅ ሻማው አልበራላት አለ ብትለው፣ብትለው ,,,, ልጀ የሁለው እየበራ ያንች ይጠፋል ለምንድን ነው ብሎ አባት ጠየቃት?
ልጅም አባየ የኔ የማይበራው እኮ አንተ ሁልጊዜ ስለምታለቅስ #እንባህ ነው የሚያጠፋብኝ አለችው።
አባት ከዛ ቀን ጀምሮ ከሀዘን ወጣ፣ከማህበርሰቡ ጋር በደስታ፣በፍቅር ተቀላቀለ፣

ስለዚህ ብዙ ማዘን እኛን ብቻ ሳይሆን ፣ የሞተውንም ሰው ነፍሱን እንርብሸዋለን ማለት ነው ። በሀዘን ላይ ብዙ መቆየት ተገቢ አይደለም ። ፆለት/ዱዓ በማርግ ለተለየን ሰው ምህርት መጠየቅ ነው።ትልቁ ነገር

ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *