ዛኑ ፒ ኤፍ ሮበርት ሙጋቤን ከፓርቲው ሊቀ መንበርነት አነሳ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 10 ፣ 2010  የዚምባቡዌ ገዥ ፓርቲ ዛኑ ፒ ኤፍ ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤን ከፓርቲው ሊቀ መንበርነት ማንሳቱን አስታወቀ።

ፓርቲው ዛሬ ባደረገው ስብሰባ ሮበርት ሙጋቤ ከፓርቲው ሊቀ መንበርነት መነሳታቸውን አስታውቋል።

ቀዳማዊ እመቤት ግሬስ ሙጋቤም ከፓርቲ አባልነታቸውና ሃላፊነት መባረራቸውም ተገልጿል።

ፓርቲው በሙጋቤ ከስልጣን የተባረሩት የቀድመሞውን ምክትል ፕሬዚዳንት ኤመርሰን መኛጋዋን ሊቀ መንበር ማድረጉንም ገልጿል።

ፓርቲው አዛውንቱን መሪ ከፕሬዚዳንትነት ስልጣናቸው ማንሳት የሚያስችለውን ሂደት መጀመሩን የሃገሪቱ የነጻነት ታጋዮች ማህበር ሃላፊ ተናግረዋል።

ፕሬዚዳንት ሙጋቤ በዛሬው እለት ከሃገሪቱ የጦር ሹማምንት ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በትናትናው እለት ፕሬዚዳንት ሙጋቤ ስልጣን እንዲለቁ የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ በሃራሬ ተካሂዶ ነበር።

 

ምንጭ፦ ቢቢሲ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *