ገዳ ትራንስፖርት በይፋ ስራ ጀመረ

ገዳ ትራንስፖርት በዛሬው እለት ስራውን በይፋ ጀምሯል።

በገዳ ትራንስፖርት ማህበር የተገዙ የተለያዩ የህዝብ ማጓጓዣ እና የጭነት ተሽከርካሪዎች የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ለማ መገርሳ በተገኙበት በይፋ ተመርቀው ስራ ጀምረዋል።

በተጨማሪም አባ ገዳዎች፣ ከፍተኛ የፌዴራል እና የክልል ባለስልጣናት፣ አርቲስቶች እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍል ተወካዮች በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ተገኝተዋል።

በዛሬው እለት በይፋ ተመርቀው አገልግሎት የጀመሩ ተሽከርካሪዎችም 20 የህዝብ ማመላለሻ እና 30 የከባድ ጭነት ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ናቸው።

gada_bus.jpg

20ዎቹ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ገዳ ባስ የሚል ስያሜ የተሰጣቸው ሲሆን፥ በጊዜያዊነት ስራቸውን በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ ከተሞች አገልግሎት በመስጠት ስራቸውን የሚጀምሩ ይሆናል።

gada_transport3.jpg

ወደ ፊት ግን በመላው ሀገሪቱ ክፍል እንዲሁም ድንበር ዘለል የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ መሆኑም ተነግሯል።

ገዳ ባስ ከሚሰማራባቸው መስመሮች ውስጥም፦

አዲስ አበባ – መቀሌ

አዲስ አበባ – ባህር ዳር

አዲስ አበባ – ጎንደር

አዲስ አበባ – ከሚሴ

አዲስ አበባ – አሶሳ

አዲስ አበባ – ጋምቤላ

አዲስ አበባ – ጂግጂጋ

አዲስ አበባ – ሰመራ

አዲስ አበባ – ሀዋሳ

አዲስ አበባ – ድሬ ዳዋ

አዲስ አበባ – ሀረር

አዲስ አበባ – ሱዳን ካርቱም

እንዲሁም ከአዲስ አበባ በመነሳት ወደ ሁሉም የክልሉ ከተሞች የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑ ተነግሯል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *