10 ሰምተው ያመያውቋቸው የሞናሊዛ እውነታዎች

10 ሰምተው ያመያውቋቸው የሞናሊዛ እውነታዎች

የታላቁ ሰአሊ የሊዎናርዶ ዳቬንቺ ውጤት የሆነችው ሞናሊዛ በአለመ ላይ በጣም ታዋቂ የሆነች እና ብዙ ግዜ የተጎበኘች ስእል ናት።መነሊዛ ለብዙ መቶ አመታት የሙሁሮች መከራከሪያ የነበረች ሲሆን አሁንም ቢሆን ብዙ ያልተፈቱ ሚስጥራዊ ጉዳዮች እንዳሏት ብዙ ሙሁራን ይስማማሉ።

እኛ ግን ከ500 አመት በላይ ስላስቆጠረው ስእል እስካሁን ካጋጠሙን እና በምርምር ከተገኘው እውነታ ከእየሱስ ክርስቶስ የደም ፅዋ የያዘው ዋንጫ መገኛ ጠቋሚ ስእል ነው ከሚለው ቲዎሪ አንስቶ እራሱን በሷ ፍቅር (በፎቶው) እስካጠፋው ሰው ድረስ ሰምተው የማያውቋቸውን እውነታዎች ይዘናል ተከታተሏቸው።

10) በሊዮናርዶ የንድፍ መፅሃፎች እና ፅሁፎች ውስጥ የሞናሊዛ ስም አንድ ግዜም ያልተጠቀሰ ሲሆን የንድፍ ስራውም ከሊዮናርዶ የንድፍ  መፅሃፎች ውስጥ አልተገኘም ። ሊዮናርዶ በስእሉም ላይ ፊርማውን ያላሰፈረ ሲሆን ቀን እና ስምም አልሰጠውም።

9) ተሞነሊዛ አስገራሚ የሆነው ሚስጥራዊ ሳቋ በ2005እኤአ ስእሉ በአምስተርዳም ዩኒቨርሲቲ ስሜትን በሚመረምር ሶፍትዌር የተጠና ሲሆን በሰፍትዌሩ ውጤት መሰረትም የሞናሊዛ ስእል 83% ደስተኛ ፣9% ስልቹ፣ 6% አስፈሪ 2% ተናዳለች ብሎ ተተንትኗል።

8) ሊዮናርዶ የሞናሊዛ ስእልን ለማሳመር አመታት የፈጀበት ሲሆን ስእሉን ጣሊያን ጀምሮት ፈረንሳይ እየኖረ ነበር የጨረሰው።ሸራው ላይ ከሞናሊዛ በፊት ሶስት ስእሎችን ስሎ እንደ ነበር የሚያሳይ ውጤት ተገኝቷል። ከበፊቶቹ ስእሎች ውስጥ አንዷ የህፃን ኮፍያ ያደረገች ሴት ነበረች።

7) ታዋቂው ሰአሊ ፓብሎፒካሶ የሞናሊዛ ስእልን በመስረቅ ወንጀል ተጠርጥሮ እስርቤት ገብቶ ነበር። በውሃላ ላይ ግን ነፃ መሆኑ ተረጋግጦ ተለቋል።

6) ሞናሊዛ ብዙ ግዜ በአጥፊዎችም አደጋ ደርሶባታል። በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1956 አንድ ሰው አሲድ ደፍቶባት የነበረ ሲሆን በዛው አመትም አንዲት ሴት በንዴት ድንጋይ ወርውራባት ተበላሽታ ነበር።ሞናሊዛ እኤአ በ1974 በቶኪዮ በምትታይበት ወቅት እንዲት ሴት ሙዚየሙ በአካል ጉዳተኞች ላይ ባለው ህግ ተናዳ የቆይ ቀለም ስፕሬይ ነፍታ ነበር። በ2009 አንዲት ራሽያዊት የፈረንሳይ ዜግነት ጠይቃ በመከልከሏ ተናዳ ከዛው ከሙዚየሙ በገዛችው የሻይ ብርጭቆ ወርውራባታለች። በአሁኑ ሰአት ግን ሞናሊዛ የአየር ፀባይን እና ጥይት በማይበሳው መስታወት ውስጥ ተቀምጣለች።

5) ዘዳቬንቺ ኮድ የተባለው መፅሃፍ ደራሲ ዳን ብራውን እንደሚጠቁመው የሞናሊዛ ስእል የእየሱስ ክርስቶስን የደም ፅዋ የተያዘበት ዋንጫ መገኛን የሚጠቁም ድብቅ መረጃ ነው ብሎ ይናገራል። በአጭሩ እመጓ ልትለው ትችላለክ።

4) ሞናሊዛ ዋጋ ሊገመትላት አይችልም።የተገባላት ኢንሹራንስ ከየትኛውም ስእል በላይ ከፍተኛ ሲሆን ከ780 ሚሊዮን ዶላር በላይ ዋጋ እንዳላት ቢነገርም የፈረንሳይ መንግስት ግን የትኛውም ዋጋ ቢቀርብለት አይሸጣትም።

3) የሞናሊዛ ሳቅ ይቀያየራል የሚባለው ስህተት ነው።ከተለያየ አቅጣጫ ስትታይ እየሳቀች ነው ? ወይስ አድለም? የሚለው ለብዙ አመታት ሙሁሮችን ያከራከረ ሲሆን በ2000እኤአ የሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የዚውሮ ሳይኒቲሰት የሆኑት ደ/ር ማርገሬት እንዳመላከቱት አተኩረን ስናያት አእምሯችን የሚመልሰው ነው እንጂ ስዕሉ በራሱ ሁለት አይነት ገጽታ የለውም ብለው ተናገረዋል።

2) የፈረንሳይ ንጉስ የነበረው ናፖሊዮን በሞናሊዛ ስእል ፍቅር ወድቆ የነበረ ሲሆን በመኝታ ቤቱ ስእሏን ሰቅሎ ለብዙ ሰአታት ስዕሉን እየተመለከተ ይቦርቅ እንደነበር ይነገራል። ለስእሉ ካለው ፍቅርም ይመስላል ሞናሊዛ ናት ተብላ ከምትገመተዋ የሊዛ ጋርዴኒ ዘር የሆነችውን ሴት ያገባው።

1) ሰዎች በሷ ፍቅር እራሳቸውን እስከማጥፋት ደርሰዋል በ1852 አንድ አርቲስት እራሱን ከአንድ ሆቴል አራተኛ ፎቅ ላይ ጥሎ ህይወቱን ያጠፋ ሲሆን ባስቀመጠው ኑዛዜ ላይም «ከአስገራሚው ፈገግታዋ ጋር በፅኑ ስታገል ኖሬያለሁ ከዚህ በውሃላ ግን መሞሞትን እመርጣለው» የሚል ፅሁፍ አስፍሮ ነበር። በ1910 እኤአ አንድ በሷ ፍቅር ያበደ ከስእሉ ፈት ሆኖ እራሱን በጥይት አጥፍቷል።

ምርጥ አስር አስገራሚ የሞናሊዛ እውነታዎች እነዚህን ይመስሉ ነበር ሃሳብ አስተያየታችሁን ኮሜንት ላይ ያስቀምጡል።ሼር ማድረግዎትንም አይዘንጉ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *