ማር ለአስም በሽታ (4 የአጠቃቀም ዘዴዎች) ተመሳሳይ መረጃዎች እንዲደርሳችሁ ላይክ እና ሼር አድርጉን

ማር ለአስም በሽታ
(4 የአጠቃቀም ዘዴዎች)

 ማር እና አዝመሪኖ

አዘገጃጀት፡-

በመጀመሪያ በአንድ የሻይ ብርጭቆ ውሃ ውስጥ አዝመሪኖ (የመጥበሻ ቅጠል) ቀላቅሎ ማፍላት፡፡ ይህ በደንብ ከተንተከተከ በኋላ ከእሳቱ ላይ በማውረድ ለጥቂት ደቂቃ ማብረድ፡፡ በአዝመሪኖ ውሃ ላይ አንድ ማንኪያ ማር ጨምሮ መበጥበጥ፤ ከዚያም መጠጣት፡፡

ይህ ፈሳሽ አስም ላለባቸው ሰዎች ፍቱን መድሃኒት ነው፡፡ በቀን ሁለት ጊዜ ወስደው ካልተሻለዎት መተኑን በመጨመር በቀን ከሶስት እስከ ስምንት ጊዜ መውሰድ ይቻላል፡፡

 ማርና ነጭ ሽንኩርት

አዘገጃጀት፡-

ሁለት ራስ ነጭ ሽንኩርት ወስዶ በሚገባ ማድቀቅ እና መፍጨት፡፡ የተፈጨውን ነጭ ሽንኩርት ከአንድ ማንኪያ ማርጋር መለወስ፡፡ በመቀተልም ይህንን ጠዋትና ማታ በቀን ሁለት ጊዜ ለአስራ አምት ቀናት ያህል መውሰድ፡፡ ይህም የሚወሰደው በተለይ የአስም ህመሙ በተቀሰቀሰበት ሰሞን ከሆነ ፍቱንነቱን በሚገባ ማረጋገጥ ይቻላል፡፡

 ማር እና ቀረፋ

አዘገጃጀት፡-

አንድ ማንኪያ ማር እና ግማሽ ማንኪያ የቀረፋ ዱቄት አብሮ መለወስና በቀን 3 ጊዜ እንደ እንክብል መውሰድ፡፡

 ማር፣ ነጭ ሽንኩርት እና የተነጠረ ቅቤ

አዘገጃጀት፡-

– 7 ማንኪያ የተፈጨ ነጭ ሽንኩርት
– 10 ማንኪያ የተነጠረ ቅቤ
– 12 ማንኪያ ማር

በአንድ ጎድጓዳ እቃ ውስጥ ማደባለቅ እና ለብ እስኪል ድረስ (በመጠኑ) ማሞቅ፡፡ በመቀጠልም ጥብቅ ክዳን ባለው ጠርሙስ ውስጥ መገልበጥ፡፡ ይህንን ውህደት በየቀኑ ከምግብ በፊት የአስሙ ሁኔታ አመርቂ ለውጥ እስኪያሳይ ድረስ መውሰድ፡፡ (በነገራችን ላይ ማርን በጣም ማሞቅ አይመከርም፡፡ ለዚህም ምክንያቱ ማር ከሚገባው በላይ በእሳት ከተመታ በውስጡ ያሉት ጠቃሚ ንጥረ ነገሮች ከጥቅም ውጭ ስለሚሆኑ ነው፡፡)

source :-scitech

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *