ሰበር ዜና: ዛሬ የ2010 ዓ.ም ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የ2 ሰዎች ህይወት አለፈ።

በ17ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ላይ የ2 ሰዎች ህይወት አለፈ

ዛሬ በተካሄደው 17ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ላይ የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስተወቀ።

ህይወታቸው ያለፉት ሁለቱ ሰዎች አንደኛው በውድድር ላይ እያለ ሌላኛው ደግሞ ውድድሩን ካጠናቀቀ በኋላ ተዝለፍለፈው መውደቃቸውን ተከትሎ መሆኑን ፖሊስ አስታውቋል።

በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ሀላፊ እና የዝግጅቱ ኮማንድ ፖስት አስተባባሪ ረዳት ኮሚሽነር ሽመልስ ሽፈራሁ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ ሁለቱ ሰዎች ከወደቁበት በፍጥነት በማንሳት በአምቡላንስ ወደ ሆስፒታል ቢወሰዱም ህይወታቸው መትረፍ አልቻለም።

ለሁለቱ ሰዎች ህይወት ህልፈት ምክንያትም የልብ ጤንነት ችግር ሊሆን እንደሚችል ከጤና ባለሙያዎች መረጃ ማግኘታቸውንም ረዳት ኮሚሽነር ሽመልስ ሽፈራሁ ገልፀዋል።

ከሁለቱ ሰዎች ህይወት ህልፈት ውጪ በውድድሩ ላይ ሌላ አደጋ አለማጋጠሙንም ተናግረዋል።
ረዳት ኮሚሽነር ሽመልስ ሽፈራሁ፥ ውድድሩ ከመነሻው ጀምሮ እስከ ፍፃሜው ድረስ ያለ ምንም የፀጥታ ችግር መካሄዱንም አስታውቀዋል።

የመነሻ ቦታ ላይም ምንም አይነት የመገፋፋት እና መጨናነቅ ችግር እንዳልነበር እና ከዚህ ጋር ተያይዞ ያጋጠመ ችግር አለመኖሩን ገልፀዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *