የማንጎ ቅጠል ለስኳር ታማሚዎች የሚሰጠው ጠቀሜታ

የማንጎ ቅጠል ለስኳር ታማሚዎች የሚሰጠው ጠቀሜታ

የስኳር በሽታ ምልክቶች እነዚህን ይመስላሉ፦

• በተደጋጋሚ ሽንት መሽናት፡፡
• ከመጠን ያለፈ የውሃ ጥም፡፡
• የፍላጎት እና ትኩረት ማጣት፡፡
• የመደንዘዝ እና የመውረር ስሜት፡፡
• የረሃብ ስሜት መጨመር፡፡
• የክብደት መቀነስ፡፡
• ድካም በእጅና እግር አካባቢ፡፡
• የአይን እይታ መጋረድ/ብዢታ፡፡
• በተደጋጋሚ በኢንፌክሽን መጠቃት፡፡
• የቁስል ማገገሚያ ጊዜ መርዘም፡፡
• ማስመለስ እና የሆድ ህመም ናቸው፡፡

የማንጎ ቅጠል ለስኳር ታማሚዎች የሚሰጠው ጠቀሜታ

1. በደም ውስጥ ያለ የስኳር መጠንን መቆጣጣር

የስኳር ህመምን ለመቆጣጣር ከሚረዱን መንገዶች ውስጥ አንዱ የደም ውስጥ ያለን የስኳር መጠን መቆጣጣር ነው።

የማንጎ ቅጠል ሰውነታችን ኢንሱሊን የማምረት አቅም እና የግሉኮስ ስርጭት እንዲጨምር የሚያደርግ ሲሆን፥ ይህ ደግሞ በደማችን ውስጥ ያለን የስኳር መጠን ለመቆጣጣር ይረዳል ነው የተባለው።

2. የኮሌስትሮል መጠንን ለመቆጣጣር

የስኳር በሽታ ታማሚ ከሆንን በሰውነታችን ውስጥ ያለ ከፍተኛ የሆነ የኮሌስትሮል መጠን የልባችን ጤንነት ላይ የከፋ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል።

ሆኖም ግን የማንጎ ቅጠል በፔሲተን፣ ቪታሚን C እና ፋይበር ንጥረ ነገሮች የበለፀገ በመሆኑ ከፍተኛ የሆነ የኮሌስትሮል መጠንን ለመቀነስ ይረዳል።

3. በስኳር ህመም ምክንያት የሚከሰት የአይን ህመም

የማንጎ ቅጠል ቪታሚን A የበለጸገ በመሆኑ ለአይን ጤንነት የሚሰጠው ጠቀሜታም ከፍተኛ መሆኑ ተነግሯል።

ከዚህ በተጨማሪም የማንጎ ቅጠል የስኳር ህመም ምልክቶች የሆኑትን በእንቅልፍ ሰዓት ቶሎ ቶሎ የመሽናት፣ ከፍተኛ የሆነ የሰውነት ክብደት መቀነስ እና የአይን እይታ መደብዘዝ ችግሮችን ለመቀነስም ይረዳል ተብሏል።

• የማንጎ ቅጠልን እንዴት መጠቀም አለብን…?

• ከማንጎ ዛፍ ላይ የተቆረጠ ከ10 እስከ 15 ቅጠል ማዘጋጀት

• ውሃ ማፍላት፤ በሚፈላው ውሃ ውስጥ የማንጎ ቅጠሉን በመጨመር አንድ ላይ እንዲፈላ በማድረግ ማሳደር

• ጠዋት ከእንቅልፋችን እንደተነሳን ሌላ ምግብም ይሁን መጠጥ ከመውሰዳችን በፊት የማንጎ ቅጠል ሻዩን መጠጣት

• ይህንን ለሁለት ወስም ሶስት ወራት ያለማቋረጥ የእለት አትለት ተግባራችን ውስጥ በማካተት በቀላሉ የስኳር ህመምን መቆጣጣር ያስችለናል ተብሏል።

• እስከዛሬ የተለያዩ የጤና መረጃዎችን ስናደርሳችሁ መቆየታችን ይታወቃል፡፡ ታዲያ አንድ ነገር አሳሰበን… ይሄውም መረጃዎቻችን ምን ያህል እየተነበቡ ነው የሚለውን ለማረጋገጥ ጥናት ላይ ስለሆንን ይህንን መረጃ አንብባችሁ የጨረሳችሁ ተከታዮቻችን በቅድሚያ መረጃውን ሼር ካደረጋችሁ በኋላ የስማችሁን የመጀመሪያ ሶስት ፊደላት በአስተያየት ሳጥኑ ውስጥ ፃፉት ከዚያ ደግሞ ላይክ አድርጉት…

source scitech

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *