የፍቅር ነገር……አስተማሪና አስገራሚ ነው ከወደዳችሁት ላይክ እና ሼር አድርጉን

አንድ ወጣት አንዲት ቆንጆ ልጅ ይወድና ፍቅሩን ለመግለፅ በጣም ይፈራል ጓደኞቹ እንዲነግራት ቢያበረታቱትም ደፍሮ ማድረግ አልቻለም
በቃ እሷን እያሰበ በትምህርቱ እየደከመ ሳቅ ጨዋታ እያስጠላው ሰውነቱ እየቀነሰ ጭንቀታም መሆኑ እጅግ ያሳሰባቸው ጓደኞቹ በስንት መከራ አግባብተው እንዲነግራት ያደርጉታል
እናም ሲፈራ ሲቸር በጣም እንደሚወዳት ይነግራታል
እሷም ቀብራራ ነገር ነበረችና እንዲህ አለችው
<<ውይ በጣም ይቅርታ እንኳን የፍቅር ጥያቄህን ልቀበልህ ይቅርና በአለም ላይ ማንን ትጠያለሽ ብባል አንተን ነው የምለው እና ይሄን ጥያቄ ደግመህ እንዳታነሳብኝ >>
ልጁም ምንም እንዳልተፈጠረ ተረጋግቶና ፈገግ ብሎ ወደ ጓደኞቹ ይመለሳል።
ጓደኞቹም ፈገግታውን ሲያዩ ልጅቷ የፍቅር ጥያቄውን እንደተቀበለችው አምነው በደስታ ተቀበሉት አንደኛው ጓደኛው <<እሺ አለችህ አይደል በጣም ደስ ይላል>> ሲለው ወጣቱ ልጅ
<<አረ በፍፁም እንደውም በአለም ላይ እንደኔ የምትጠላው ሰው እንደሌለ ነው የነገረችኝ>>አላቸው ጓደኞቹ ግራ ተጋብተው
<<ታድያ እንዴት አላዘንክም እንዴት አልተከፋህም?>> አሉት እሱም ረጋ ብሎ እንዲህ ሲል መለሰላቸው
<<ለምን እከፋለሁ ለምንስ አዝናለሁ? እኔ እኮ ያጣሁት በአለም ላይ ከምንም በላይ የምትጠላኝን ልጅ ነው። እሷ ግን ያጣችው በአለም ላይ ከምንም በላይ የሚወዳትን ሰው ነው ስለዚህ እኔ ሳልሆን ማዘንም መከፋትም ያለባት እሷ ናት>> አላቸው።
ይሄ ታሪክ የሁላችንም ነው አንድ የምንወደው ሰው ጥላቻውን ሲያሳየን ወይም ሲርቀን እንከፋለን እናዝናለን እናለቅሳለን ግን ይሄን ማድረግ ያለበት ያ ትቶን የሄደ ሰው ነው እንጂ እኛ አልነበርንም።
መልካም እለተ ቅዳሜ ጓዶች ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *